10 ትልሟን በውሃ ታረሰርሳለህ፤ቦይዋን ታስተካክላለህ፤በካፊያ ታለሰልሳለህ፤ቡቃያዋንም ትባርካለህ።
11 ለዘመኑ በጎነትህን ታጐናጽፈዋለህ፤ሠረገላህም በረከትን ተሞልቶ ይፈስሳል።
12 የምድረ በዳው ሣር እጅግ ለመለመ፤ኰረብቶችም ደስታን ተጐናጸፉ።
13 ሜዳዎች መንጋ በመንጋ ሆኑ፤ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፤እልል ይላሉ፤ ይዘምራሉም።