3 ኀጢአት ባጥለቀለቀን ጊዜ፣አንተ መተላለፋችንን ይቅር አልህ።
4 አንተ የመረጥኸው፣ ወደ ራስህ ያቀረብኸው፣በአደባባይህም ያኖርኸው ምስጉን ነው!ከተቀደሰው መቅደስህ፣ከቤትህም በረከት እንረካለን።
5 እግዚአብሔር አዳኛችን ሆይ፤በጽድቅ ድንቅ አሠራር መልስልን፤አንተ ለምድር ዳርቻ ሁሉ፣በርቀት ላለውም ባሕር ተስፋ ነህ።
6 ተራሮችን በብርታትህ መሠረትህ፤ኀይልንም ታጥቀሃል።
7 አንተ የባሕሮችን ማስገምገም፣የማዕበላቸውን ፉጨት፣የሕዝቦችንም ሁከት ጸጥ ታደርጋለህ።
8 ርቀው በምድር ዳርቻ ያሉት ከድንቅ ሥራህ የተነሣ ይደነግጣሉ፤የንጋትንና የምሽትን መምጫዎች፣በደስታ እልል እንዲሉ ታደርጋቸዋለህ።
9 ምድርን ትጐበኛለህ፤ ታጠጣለህም፤እጅግ ታበለጽጋታለህም።ለሰዎች እህልን ይለግሱ ዘንድ፣የእግዚአብሔር ወንዞች ውሃን የተሞሉ ናቸው፤አንተ እንዲህ እንዲሆን ወስነሃልና።