3 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ይህን አድርጌ ከሆነ፣በደልም በእጄ ከተገኘ፣
4 በጎ ለዋለልኝ ክፉ መልሼ ብሆን፣ጠላቴንም በከንቱ ዘርፌ ከሆነ፣
5 ጠላቴ አሳዶ ይያዘኝ፤ሕይወቴን ከምድር ይቀላቅል፤ክብሬንም ከዐፈር ይደባልቅ። ሴላ
6 እግዚአብሔር ሆይ፤ በመዓትህ ተነሥ፤በቍጣ በተነሡብኝ ላይ ተነሥ፤አምላኬ ሆይ፤ ንቃ፤ ትእዛዝም አስተላልፍ!
7 የሕዝቦች ጉባኤ ይክበብህ፤አንተም ከላይ ሆነህ ግዛቸው፤
8 እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል። እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ጽድቄ ፍረድልኝ፤ልዑል ሆይ፤ እንደ ቅን አካሄዴ መልስልኝ።
9 ልብንና ኵላሊትን የምትመረምር፣ጻድቅ አምላክ ሆይ፤የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ፤ጻድቁን ግን አጽና።