12 አምላክ ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤አምላኬ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
13 ባላንጣ የሆኑብኝ ይፈሩ፤ ይጥፉም፤ሊጐዱኝ የሚፈልጉ፣ንቀትንና ውርደትን ይከናነቡ።
14 እኔ ግን ሁል ጊዜ ተስፋ አደርጋለሁ፤በምስጋና ላይ ምስጋና አቀርብልሃለሁ።
15 አንደበቴ ስለ ጽድቅህ፣ቀኑን ሙሉ ስለ ማዳንህ ይናገራል፤ማቆሚያ ልኩንም አላውቅም።
16 መጥቼ የጌታ እግዚአብሔርን ብርቱ ሥራ ዐውጃለሁ፤የአንተን ጽድቅ ብቻ እናገራለሁ።
17 አምላክ ሆይ፤ አንተ ከልጅነቴ ጀምረህ አስተማርኸኝ፤እኔም እስከ ዛሬ ድረስ ድንቅ ሥራህን ዐውጃለሁ።
18 አምላክ ሆይ፤ ሳረጅና ስሸብትም አትተወኝ፤ክንድህን ለመጭው ትውልድ፣ኀይልህን ኋላ ለሚነሣ ሕዝብ ሁሉ፣እስከምገልጽ ድረስ።