20 ብዙ መከራና ጭንቅ ብታሳየኝም፣ሕይወቴን እንደ ገና ታድሳለህ፤ከምድር ጥልቅም፣እንደ ገና ታወጣኛለህ።
21 ክብሬን ትጨምራለህ፤ተመልሰህም ታጽናናኛለህ
22 አምላኬ ሆይ፤ ስለ ታማኝነትህ፣በበገና አመሰግንሃለሁ፤የእስራኤል ቅዱስ ሆይ፤በመሰንቆ እዘምርልሃለሁ።
23 ዝማሬ በማቀርብልህ ጊዜ ከንፈሮቼ በደስታ ይሞላሉ፤አንተ የተቤዠሃትም ነፍሴ እልል ትላለች።
24 አንደበቴ ስለ ጽድቅህ፣ቀኑን ሙሉ ያወራል፤የእኔን መጐዳት የሚፈልጉ፣አፍረዋልና፤ ተዋርደዋልም።