5 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ተስፋዬ፤ከልጅነቴም ጀምሮ መታመኛዬ ነህና።
6 ከተወለድሁ ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፤ከእናቴ ማሕፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ፤አንተ የዘወትር ምስጋናዬ ነህ።
7 ብዙዎች እንደ ጒድ አዩኝ፤አንተ ግን ጽኑ አምባዬ ነህ።
8 ቀኑን ሙሉ ክብርህን ያወራ ዘንድ፣አፌ በምስጋናህ ተሞልቶአል።
9 በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤ጒልበቴም ባለቀበት ጊዜ አትተወኝ።
10 ጠላቶቼ ተነጋግረውብኛልና፤ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ በአንድ ላይ አሢረዋል፤
11 እነርሱም፣ “እግዚአብሔር ትቶታል፤የሚያስጥለው የለምና፣ ተከታትላችሁ ያዙት” አሉ።