2 በመከራዬ ቀን እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤በሌሊትም ያለ ድካም እጆቼን ዘረጋሁ፤ነፍሴም አልጽናና አለች።
3 አምላክ ሆይ፤ አንተን ባሰብሁ ቍጥር ቃተትሁ፤ባወጣሁ ባወረድሁም መጠን መንፈሴ ዛለች። ሴላ
4 ዐይኖቼ እንዳይከደኑ ያዝሃቸው፤መናገር እስኪሳነኝ ድረስ ታወክሁ።
5 የድሮውን ዘመን አሰብሁ፤የጥንቶቹን ዓመታት አውጠነጠንሁ።
6 ዝማሬዬን በሌሊት አስታወስሁ፤ከልቤም ጋር ተጫወትሁ፤ መንፈሴም ተነቃቅቶ እንዲህ ሲል ጠየቀ፦
7 “ለመሆኑ፣ ጌታ ለዘላለም ይጥላልን?ከእንግዲህስ ከቶ በጎነትን አያሳይምን?
8 ምሕረቱስ ለዘላለም ጠፋን?የገባውስ ቃል እስከ ወዲያኛው ተሻረን?