34 እርሱ በገደላቸው ጊዜ ፈለጉት፤ከልባቸው በመሻትም ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ።
35 እግዚአብሔር ዐለታቸው፣ልዑል አምላክ ቤዛቸው እንደሆነ አሰቡ።
36 ነገር ግን በአፋቸው ሸነገሉት፤በአንደበታቸው ዋሹት።
37 ልባቸው በእርሱ የጸና አልነበረም፤ለኪዳኑም ታማኞች አልነበሩም።
38 እርሱ ግን መሓሪ እንደ መሆኑ፣በደላቸውን ይቅር አለ፤አላጠፋቸውም፤ቊጣውን ብዙ ጊዜ ገታ፤መዓቱንም ሁሉ አላወረደም።
39 ወጥቶ የማይመለስ ነፋስ፣ሥጋ ለባሾች መሆናቸውን አሰበ።
40 በምድረ በዳ ስንት ጊዜ ዐመፁበት!በበረሓስ ምን ያህል አሳዘኑት!