1 እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው!ክብርህ ከሰማያት በላይ፣ከፍ ከፍ ብሎአል።
2 ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ ሕፃናት አፍ፣ምስጋናን አዘጋጀህ፤ከጠላትህ የተነሣ፣ባላንጣንና ቂመኛን ጸጥ ታሰኝ ዘንድ።
3 የጣቶችህን ሥራ፣ሰማያትህን ስመለከት፣በስፍራቸው ያኖርሃቸውን፣ጨረቃንና ከዋክብትን ሳይ፣
4 በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?ትጠነቀቅለትም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?
5 ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው፤የክብርንና የሞገስን ዘውድ አቀዳጀኸው።
6 በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምኸው፤ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛህለት፤