1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምድርህ በጎ ውለሃል፤የያዕቆብንም ምርኮ መለስህ።
2 የሕዝብህን በደል ይቅር አልህ፤ኀጢአታቸውንም ሁሉ ሸፈንህ። ሴላ
3 መዓትህን ሁሉ አራቅህ፤ከብርቱ ቍጣህም ተመለስህ።
4 መድኀኒታችን የሆንህ አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤በእኛ ላይ የተቃጣውን ቍጣህን መልሰው።
5 የምትቈጣን ለዘላለም ነውን?ቊጣህስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይቀጥላልን?
6 ሕዝብህ በአንተ ሐሤት ያደርግ ዘንድ፣መልሰህ ሕያዋን አታደርገንምን?