4 መድኀኒታችን የሆንህ አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤በእኛ ላይ የተቃጣውን ቍጣህን መልሰው።
5 የምትቈጣን ለዘላለም ነውን?ቊጣህስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይቀጥላልን?
6 ሕዝብህ በአንተ ሐሤት ያደርግ ዘንድ፣መልሰህ ሕያዋን አታደርገንምን?
7 እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አሳየን፤ማዳንህን ለግሰን።
8 እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፤ለሕዝቡ፣ ለቅዱሳኑ ሰላምን ይናገራልና፤ዳሩ ግን ወደ ከንቱ ምግባራቸው አይመለሱ።
9 ክብሩ በምድራችን ይኖር ዘንድ፣ማዳኑ ለሚፈሩት በእርግጥ ቅርብ ነው።
10 ምሕረትና ታማኝነት ተገናኙ፤ጽድቅና ሰላም ተቃቀፉ።