1 ስለ እግዚአብሔር ምሕረት ለዘለላለም እዘምራለሁ፤በአፌም ታማኝነትህን ከትውልድ እስከ ትውልድ እገልጻለሁ።
2 ምሕረትህን ለዘላለም እንደምትመሠርት፣ታማኝነትህንም በሰማይ እንደምታጸና እናገራለሁና።
3 አንተም እንዲህ ብለሃል፤ “ከመረጥሁት ጋር ኪዳን ገብቻለሁ፤ለባሪያዬ ለዳዊት ምያለሁ፤
4 ‘ዘርህን ለዘላለም እተክላለሁ፤ዙፋንህንም ከትውልድ እስከ ትውልድ አጸናለሁ።’ ” ሴላ