8 ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር ስጡ፤ቍርባንን ይዛችሁ ወደ አደባባዩ ግቡ።
9 በተቀደሰ ውበት ለእግዚአብሔር ስገዱ፤ምድር ሁሉ፤ በፊቱ ተንቀጥቀጡ።
10 በሕዝቦች መካከል፣ “እግዚአብሔር ነገሠ” በሉ፤ዓለም በጽኑ ተመሥርታለች፤ አትናወጥም፤እርሱ ለሕዝቦች በእኩልነት ይፈርዳል።
11 ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድርም ሐሤት ታድርግ፤ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ ያስተጋባ፤
12 መስኩና በላዩ ያለው ሁሉ ይፈንጥዝ፤ያን ጊዜ የዱር ዛፎች ሁሉ በደስታ ይዘምራሉ፤
13 እርሱ ይመጣልና በእግዚአብሔር ፊት ይዘምራሉ፤በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል፤በዓለም ላይ በጽድቅ፣በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል።