1 እግዚአብሔር ነገሠ፤ ምድር ደስ ይበላት፤በሩቅ ያሉ የባሕር ጠረፎች ሐሤት ያድርጉ።
2 ደመናና ጥቅጥቅ ያለ ጭጋግ በዙሪያው አለ፤ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።
3 እሳት በፊቱ ይሄዳል፤በዙሪያው ያሉትንም ጠላቶቹን ይፈጃል።
4 መብረቁ ዓለምን አበራ፤ምድርም አይታ ተንቀጠቀጠች።
5 ተራሮች በእግዚአብሔር ፊት፣በምድርም ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ።
6 ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤ሕዝቦችም ሁሉ ክብሩን ያያሉ።