1 ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ አቅርቡ፤እርሱ ድንቅ ነገሮችን አድርጎአልና፤ቀኝ እጁ፣ ቅዱስ ክንዱም፣ማዳንን አድርገውለታል።
2 እግዚአብሔር ማዳኑን አሳወቀ፤ጽድቁንም በሕዝቦች ፊት ገለጠ።
3 ለእስራኤል ቤት ምሕረቱን፣ታማኝነቱንም አሰበ፤የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ፣የአምላካችንን ማዳን አዩ።
4 ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ውዳሴን አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፤
5 ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት፤በበገናና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩለት፤
6 በእንቢልታና በመለከት ድምፅ፣በንጉሡ በእግዚአብሔር ፊት እልል በሉ።
7 ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ፣ዓለምና የሚኖሩባትም ሁሉ ያስገምግሙ።