1 እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤በአማልክት ፊት በመዝሙር እወድስሃለሁ።
2 ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤ስለ ምሕረትህና ስለ ታማኝነትህ፣ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፤ስምህንና ቃልህን፣ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ አድርገሃልና።
3 በጠራሁህ ቀን መልስ ሰጠኸኝ፤ነፍሴን በማደፋፈርም ብርቱ አደረግኸኝ።
4 እግዚአብሔር ሆይ፤ የአፍህን ቃል በሰሙ ጊዜ፣ የምድር ነገሥታት ሁሉያመስግኑህ።
5 የእግዚአብሔር ክብር ታላቅ ነውና፣ስለ እግዚአብሔር መንገድ ይዘምሩ።
6 እግዚአብሔር በከፍታ ስፍራ ቢሆንም፣ ዝቅ ያለውን ይመለከተዋል፤ትዕቢተኛውን ከሩቅ ያውቀዋል።
7 በመከራ መካከል ብሄድም፣አንተ ሕይወቴን ትጠብቃታለህ፤በጠላቶቼ ቍጣ ላይ እጅህን ትዘረጋለህ፤በቀኝ እጅህም ታድነኛለህ።
8 እግዚአብሔር በእኔ ላይ ያለውን ዐላማ ይፈጽማል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ ለዘላለም ነው።የእጅህንም ሥራ ቸል አትበል።