1 እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኅኔ ነው፤የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር ለሕይወቴ ዐምባዋ ነው፤ማንን እፈራለሁ?
2 ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ፣ክፉዎች ገፍተው በመጡ ጊዜ፣ጠላቶቼና ባላጋራዎቼ በተነሡብኝ ጊዜ፣እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ።
3 ሰራዊት ቢከበኝ እንኳ፣ልቤ አይፈራም፤ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ፣ልበ ሙሉ ነኝ።
4 እግዚአብሔርን አንዲት ነገር እለምነዋለሁ፤እርሷንም እሻለሁ፤ይኸውም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ውበት አይ ዘንድ፣በመቅደሱም ሆኜ አሰላስል ዘንድ ነው።
5 በመከራ ቀን፣በድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛልና፤በድንኳኑም ጓዳ ይሸሽገኛል፤
6 በዚህ ጊዜ በዙሪያዬ ባሉ ጠላቶቼ ላይ፣ራሴ ከፍ ከፍ ይላል፤በድንኳኑም ውስጥ የእልልታ መሥዋዕት እሠዋለሁ፤ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፤እዘምርለታለሁም።
7 እግዚአብሔር ሆይ፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ስማኝ፤ራራልኝ፤ ስማኝም።