1 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን መጠጊያ አደረግሁ፤ከቶም አልፈር።
2 በጽድቅህ ታደገኝ፤ አስጥለኝም፤ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ አድነኝም።
3 ምንጊዜም የምሸሽበት፣መጠጊያ ዐለት ሁነኝ፤አንተ ዐለቴ ምሽጌ ነህና፣ታድነኝ ዘንድ ትእዛዝህ ይውጣ።
4 አምላኬ ሆይ፤ ከክፉ እጅ፣ከግፈኛና ከጨካኝ መዳፍ አውጣኝ።
5 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ተስፋዬ፤ከልጅነቴም ጀምሮ መታመኛዬ ነህና።
6 ከተወለድሁ ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፤ከእናቴ ማሕፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ፤አንተ የዘወትር ምስጋናዬ ነህ።